NEWS
የመሬት መደርመስና ጎርፍ ባስከተለው የንብረትና ህይወት አደጋ እስካሁን የተገኙ የሟቾች ቁጥር 107 መድረሱንና ከዛም ሊጨምር እንደሚችል ተጠቆመ፡፡(መጋቢት 3 ቀን 2018ዓ.ም ፍኖት ሚዲያ)
Written by Finote Media
5 MIN READ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጋሞ ዞን ጋጮ ባባ ወረዳ ማዞ ዶይሳ ቀበሌ በደረሰ የመሬት መደርመስና ጎርፍ ባስከተለው የንብረትና ህይወት አደጋ እስካሁን የተገኙ የሟቾች ቁጥር 107 መድረሱንና፡ አሁንም አስከሬን የመፈለግ ስራ የቀጠለ ቢሆንም በቁፋሮው የሰው ህይወት ለማትረፍ ያለው ተስፋ መሟጠጡን የሟቾች ቁጥርም ከተጠቀሰው በላይ ሊያሻቅብ እንደሚችል ከስፍራው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡ በደቡብ ኢትዮጵያ በተደጋጋሚ ግዜ እየተከሰተ ያለው የተፈጥሮ የመሬት መንሸራተት አደጋ በንብረትና በህይወት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን ከግምት በማስገባት አደጋዎችን ለመከላከል የሚያስችሉ ቅድመ አደጋ መለያ ቴክኖሎጂዎችን መጠቀም፣ መሠል ተፈጥሯዊ አደጋዎች እንዳይፈጠሩ የሚያደርጉ የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች ላይ የሚመለከተው አካል ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይገባል፡፡
#Ethiopian#Nashville
0
