ዜና አድዋ
130ኛው የአድዋ ድል በዓል በናሽቪል ቴነሲ ታስቦ ዋለ
Written by Finote Media
5 MIN READ

በሰሜን አሜሪካ ቴነሲ ስቴት ናሽቪል ከተማ የኢትዮጵያውያን ማህበር በናሽቪል ኢማና ያዘጋጀው የአድዋ 130ኛው የድል በዓል መታሰቢያን ምክንያት በማድረግ የእግር ጉዞ ተደረገ፡፡በእለቱ የኢማና ሊቀመንበር ዶ/ር ሀና ዓለሙ ይህንን የአድዋ ድል በዓል ከአዳራሽ አውጥቶ በአደባባይ ለማሰብ የተደረገበት ዋና ምክንያት የአድዋ ዘማች ጀግኖች እናትና አባቶቻችን በዘመኑ ያደረጉትን ጉዞ ለማሰብና በአይነ ህሊናችን ያን እያሰብን የተከፈለልን መስዋዕትነት ምን ያህል ጥልቅ እንደነበር ለመረዳት ታስቦ መሆኑን በጉዞው ለተሳተፉ የአካባቢው ነዋሪዎች ገለፃ በማድረግ ጉዞውን አስጀምረዋል፡፡ከጉዞው መጠናቀቅ በኋላም አቶ ፀሀዬ ደመቀ በአድዋ ድል ዙሪያ እና ታሪካዊ ዳራ አጭር ገለጻ አድርገዋል፡፡በመጨረሻ ሀገርና ታሪክ በትውልድ ቅብብሎሽ የሚቀጥል በመሆኑ የኛን ፈለግ መከተል ያለበት ተተኪው ትውልድ ነው፡፡ እራሱን በእውቀት እያነጸ ታሪኩን ሊያቆይ ይገባል በማለት ለታዳጊዎች የኢትዮጵያን ባንዲራ ያስረከቡ ሲሆን ፤በቦታው በመገኘት የጉዞው አካል በመሆን ተሳታፊ ለነበሩ የምስጋና ንግግር በዶ/ር እናውጋው ቀርቦ የፕሮግራሙ ፍጻሜ ሆኗል፡፡
0
