በኢትዮጵ በመንግሥት በጀት የሚተዳደረው መገናኛ ብዙኃን ፍትሀዊነት በጎደለው መልኩ ለገዥው ፓርቲ ያደላ ዘገባን እንደሚሰራ ተገለፀ፡፡

“ምርጫ 2018 – ኢትዮጵያ ኢንሳይደር”በሚል ርዕስ በወጣው የዳሰሳ ጥናት ሪፖርት ከጥር 16 እስከ የካቲት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ባለው የአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን (ኢቲቪ) በምሽት ሁለት ሰዓት ዜናዎቹ ያቀረባቸውን ዘገባዎችን መመርመሩን ጠቅሶ ኢቲቪ ለሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች ተመጣጣኝ እና ፍትሓዊ የዘገባ ሽፋን እንዳልሰጠ ማረጋገጥ ችያለሁ ብሏል ኢትዮጵያ ኢንሳይደር፡፡ ኢትዮጵያን ኢንሳይደር የቀድሞዋ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ “ዛሬ እዚህ የምትቀርፁን የመንግሥት ሚዲያዎች… የመንግሥት ባለሥልጣናት ኮታቸው ላይ የተሰካው ማይክራፎን የማይወልቅ ይመስል ሌት ተቀን የእነሱን ካምፔን እና ቅስቀሳ ስታስተላልፉ ቆይታችሁ የተቃዋሚዎችን 10 እና 15 ደቂቃ ማድረጋችሁ ፍትሐዊነታችንን አጉድሎብናል”በማለት ሐምሌ 3፣ 2013 ዓም፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የ6ኛውን አገር ዐቀፍ ምርጫ ይፋ ባደረገበት ወቅት የተናገሩትን ንግግር እንደ ደጋፊ አስረጅ ሀሳብ ጠቅሶ ከፍተኛ ተደራሽነት ያላቸው የመንግሥት ሚዲያዎች የምርጫ አዘጋገብ የምርጫው ፍትሐዊነት ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ በመረዳት፣ ይህንን ዳሰሳ ለማዘጋጀት የምርመራው መነሻ (መግፍዔ) እንደሆነው ጠቅሷል። https://ethioelections.com/የኢትዮጵያ-ቴሌቪዥን-የቅድመ-ምርጫ-2018-አዘጋ/
