ዜና (መጋቢት 05 ቀን 2018ዓ.ም ፍኖት)
ለሁለት ቀን የተዘጋጀው ልዩ መርሀግብር ተጀመረ።
Written by Finote Media
5 MIN READ

በናሽቪል ሐመረ ኖህ ኪዳነምህረት ወቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን የአብይ ፆም እኩሌታ ደብረዘይት በዓልን ምክንያት በማድረግ የተዘጋጀው የሁለት ቀን ልዩ መርሀግብር በዛሬው እለት ማለትም (መጋቢት 05 ቀን 2018ዓ.ም ፍኖት) ተጀመረ። በመክፈቻው ቀን ፕሮግራም ካህናት ፣ቤተክርስቲያንን የሚያገለግሉ ዘማርያን እና በናቪልና አካባቢው የሚገኙ ምእመናን የታደሙ ሲሆን በእለቱ ፀጋው የበዛላቸው ተጋባዥ የቤተክርስቲያን አባቶች የወንጌል ትምህርት እንዲሁም በዝማሬ ቤተክርስቲያንን የሚያገለግሉ ዘማርያን በበገና የታጀበ ዝማሬዎችን አሰምተዋል። ይህ መንፈሳዊ መርሀግብር በተያዘለት ፕሮግራም መሰረት ነገ መጋቢት 7-2018 በእለተ ደብረዘይት ከቅዳሴ በኃላም እንደሚቀጥል ይጠበቃል።
0
